Announcement የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከክላስተር ኮሌጆች ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራረመ ።

የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከክላስተር ኮሌጆች ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራረመ ።

13th January, 2026

የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከክላስተር ኮሌጆች ማለትም ከአራዳ፣ ከሰላም ፣ልደታ እና ከየካ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እና የጋራ የመግባቢያ ሰነድ (MOU) ተፈራረመ ። ኮሌጁ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው በዚህ መድረክ ላይ በኮሌጆቹ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር፣ የሀብት ክፍፍልን ለማሳለጥ እና ወቅቱን የዋጀ ስልጠና በመስጠት ብቁ እና ተወዳዳሪ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለገበያ ለማቅረብ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በተጨማሪም የልምድ ልውውጥ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ዙሪያ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ ፣ የሀብት አጠቃቀም ላይ ያሉ የላብራቶሪ፣ የዎርክሾፕ እና የሰው ኃይል አቅምን በጋራ በመጠቀም የሥልጠና ጥራትን ማሳደግ ፣ የገበያ ትስስር ሰልጣኞች ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ በቀጥታ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑ ተገልፀዋል ። የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአራዳ፣ ከሰላም ፣ልደታ እና ከየካ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር የተደረገው ይህ የሥራ ስምምነት (MOU)፣ ኮሌጆቹ በሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅት እና በተግባራዊ ሥልጠና ወቅት በቅንጅት እንዲሰሩ ሕጋዊ ማዕቀፍ ከመፍጠሩም ባሻገር በተለይ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://vm.tiktok.com https://t.me/EntotoPtc1917 https://youtube.com/@entototms https://www.facebook.com ከኮሚኒኬሽን ቡድን

.

Copyright © All rights reserved.

Created with