ሐምሌ 30/2017ዓ.ም
በኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሁለት ዘርፎች ላይ ለተዋቀሩ 4 ቡድኖች ኦረንቴሽን ተሰጠ።
በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተዋቀሩት ቡድኖች የቴክኖሎጂ ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በኢንተርፕራይዞች እና በኢንደስትሪዎች የሚፈለጉ የቴክኖሎጂ አይነቶችን ይለያሉ ፤ የተለዩቱ ቴክኖሎጂዎች ተመርተው ወደ ገበያው ይገባሉ።
ሌላኛው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ቡድን በ2017በጀት ዓመት በኮሌጁ ተቀድተው የተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች በኢንተርፕራይዙ ላይ ያመጣው ለውጥ /ያስገኘው ፋይዳ ምንድነው ? የሚለውን የሚያጠና ሲሆን ዓላማውም በቀደመው ስራ ላይ የነበረውን ክፍተት በመለየት ክፍተቱን የሚሞላና የቀጣዩን ለማሻሻል ማገዝ ነው ።
በተመሳሳይ በዚህ ክፍል ላይ የኢንተርፕራይዝ ድጋፍን የሚመለከት ሲሆን በዚህ ዘርፍም ሁለት ቡድኖች ተዋቅረዋል ። የመጀመሪያው ቡድን በ181 የነባር ኢንተርፕራይዞች የድጋፍ ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ሲሆን ኢንተርፕራይዞቹ ከአራቱም የድጋፍ ማዕቀፍ በየትኛው ላይ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ይፈልጋሉ? የሚለውን በጥናት በበመለስ በፍላጎታቸው ላይ ተመስርቶ ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል ነው ።
ሁለተኛው ቡድን በLMIS ላይ የተመዘገቡትን 1664 ኢንተርፕራይዞች ከክፍለ ከተማ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የአካል ርክክቡን ፎርም በማስሞላት የሚያከናውን ቡድን ሲሆን ኢንተርፕራይዞቹ ለ2018 ዓ.ም የሚፈልጉትን የድጋፍ አይነት እና መቼ እንዲደገፉ ይፈልጋሉ ? የሚለውን በድጋፍ አይነትና ግዜ በመለየት ያስቀምጣል ።
በአጠቃላይ በነዚህ ሁለት ዘርፎች ውጤታማ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የኢንተር ፕራይዝ ድጋፍ ለማድረግ ከተለያዩ ስልጠና ዘርፎች የተውጣጡ አሰልጣኞች ፣ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ የተወከሉ ባለሙያዎች በተገኙበት የኮሌጁ ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን አቶ ወንድም ሲያኝረኝ መኮንን እና የዘርፍ ኃላፊዎች የየዘርፋቸውን ሰፊ ማብራሪያና የጋራ የስራ ስምሪት ሰጥተውበታል ።
ኮሙኒኬሽን ቡድን።