Announcement ሐምሌ 11/2017ዓ.ም

ሐምሌ 11/2017ዓ.ም

19th July, 2025

የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከባለድርሻ አካላቱ ጋር ዕቅድን መሠረት ያደረገ ውይይት አካሄደ። 

ኮሌጁ ከአጠቃላይ ትምህርት፣ ከከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት፣ ከምዘና ማዕከል ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ያደረገው ውይይት በበጀት ዓመቱ የኮሌጁን የስራ አፈጻጸም በተመለከተ ሲሆን ትኩረት የተደረገበት ደግሞ በአቅራቢያው ካሉ የመደበኛ ትምህርት ቤቶች ጋር መግባባት በተደርሶባቸውና ስለተሰሩ ስራዎች እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በቀጣይ መሠራት ስላለባቸው ስራዎችም በውይይቱ የተካተቱ  እንደነበርም እንደዚሁ። 

በውይይቱ ላይ የተገኙት ዋና ዲን አቶ አብዱልበር መሐመድ ለእንግዶቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ከዚህ በፊት በተፈጠሩት መድረኮች እርስ በርስ የመተዋወቅና ኮሌጁ ባለው አቅም በአዲሱ ካሪኩለም ለተጀመረው የሞያ ስልጠና አጋዥ የሆኑ ቁሳቁሶችን ማጋራታቸውን አስታውሰው  አሁን ደግሞ በታቀደና  በተጠናከረ መልኩ መስራት በጋራ ተጠቃሚ እንሚያደርግ ጠቁመዋል ። 

በትስስር ስራዎችን ለመስራት በቅድሚያ በእቅዳችን ላይ አካተን የምናዘጋጃቸውና ለተግባራዊነቱም ያላሰለሰ ጥረት የምናደርግባቸው ሊሆኑ እንደሚገባም በመልዕክታቸው አካተዋል። 

በተያያዘም ዲኑ ኮሌጁ ይህንን ፕሮግራም በተሻለና አጠናክሮ እንደሚሰራበትም አሳስበው በ2017ዓ.ም ከኮሌጁ ጋር በነበራቸው የትስስር ስራ አንጻር ከት/ቤቶችና ምዘና ማዕከላት ጋር የነበረውን ግንኙነት በደረጃ ማስቀመጣቸውንም ጠቁመዋል ። በዚህ ደረጃ መሠረትም ኮሌጁ እውቅና በመሥጠት የባለድርሻዎችን ተሳትፎ እንደሚያበረታታ ጨምረው ገልፀዋል። 

የዕቅድ አፈጻጸሙን ሪፖርትና ለቀጣዩ የሥራ ዘመን የዕቅድ መነሻ ሃሳቡን ለውይይት ያቀረቡት የኮሌጁ ስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ደመላሽ ተስፋዬ ናቸው ። 

በውይይቱ በአዎንታ ከተነሱት ነጥቦች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የሰልጣኞች ቅበላ መጨመር የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑ ሲሆን በአሉታ ከተነሱት እና የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲስተካከል የተጠየቀው  የምዘና ጉዳይ ይገኝበታል።

በመቀጠልም ኮሌጁ ፈቃድ ያገኘባቸውን ኢንተርፕራይዞች እና ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡትን ምርትና አገልግሎት ለባለድርሻ አካላቱ በማስተዋወቅ ባለድርሻ አካላቱ የሚመሯቸው የመንግስት መስሪያቤቶች የነዚህ ምርትና አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተጠይቋል። ኮሌጁም ተወዳዳሪ የሆኑ ምርትና አገልግሎት  በተቀመጠለት የጥራት ደረጃና ጊዜ ማስረከብ የሚችል መሆኑን ተሳታፊዎች እንዲያውቁ መረጃ ተላልፏል ። 

በመጨረሻም በቀረበው ሪፖርት መነሻነት ከእንጦጦ አምባ፣ ከድል በርና ከከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ሐሳብ አስተያየት ቀርቦ በቀጣይ ሰልጣኝ ቅበላ ላይ እና በሙያ ትምህርት ስልጠና አሰጣጥ ላይ ተጠናክሮ ለመስራት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥረትና ትብብር ሊኖር እንደሚገባ  ተጠቁሟል።  ለአጠቃላይ ስራውም እንዲረዳ በግልና በጋራ በሚወስዷቸው ሃላፊነቶች ላይ ባለድርሻ አካላቱ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። 

             ኮሙኒኬሽን ቡድን

.

Copyright © All rights reserved.

Created with