Announcement ተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከመሰንበቻው

ተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከመሰንበቻው

08th July, 2025

ከኮሌጁ የምዕተ ዓመት አከባበር እና ከስያሜ ለውጡ ጋር በተያያዘ  በርከት ያሉ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል ። 

በመጠናቀቅ ላይ ያለው ዋናው በር የተመለሰውን ነባሩን ስያሜ ለመሸከም እና የመግቢያ አገልግሎት ለማስተናገድ ብቻ የተዘጋጀ ግንባታ አይደለም ፤ ወደ ግቢው ከመዝለቅዎ በፊት ከውስጥ የሚጠብቆትን ታሪካዊ ህንፃ ምን እንደሚመስል ለማመላከት ጭምር ታስቦበት የተዘጋጀ መሆኑን ዲዛይኑን  ያዘጋጀው እና የግንባታ ክትትሉን የሚያከናወነው የኮሌጁ  አሠልጣኝ ሚኪያስ ይርጋለም ይገልጻል ። ሚኪያስ በመቀጠል በከርቭ መልክ የተሰራውና ቄንጠኛው የመግቢያ በር በሁለት ቋሚዎች መካከል የሚገኝ እና በሚያማምሩ ጥርብ ድንጋዮች የተገነባ ነው። ይህም ጥንካሬውን፥ ታሪካዊነቱን፥ ወቅታዊነቱን እና ቀጣይነቱን ያሳያል ይላል። እንደ ሚክያስ ገለጻ የከርቭ ቅርጽ  በጥበብ ቋንቋ የፈጠራስሜትን ለማበረታታት፣ እድገትን ለማመላከት ያገለግላል ይላል። ው 

በዚህ መልክ የተሰራው ዋና በር ጠንከር ያለ ወጭ/4.5 ሚልየን ብር እንደሚገመት ተጠቁሟል። ይህ ወጪ ሙሉ በሙሉ በቀድሞ ተማሪዎች ማሀበር እንደተሸፈነም እንደዚሁ። ሚኪያስ በዚህ አጋጣሚ ማህበሩን በራሱና በኮሌጁ ስም ማመስገን ይፈልጋል ፤ ተገቢም ነው። ማህበሩ የሚያደርገዉ ድጋፍ በዚህ ብቻ የተወስነ አይደለም በፋይናንስም በማቴሪያልም ኮሌጁን ሲያግዝ ቆይቷል። አሁንም ባለ ሦስት ወለል ህንፃ ለማሰራት በጥረት ላይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል ። 

በግንባታ ሂደት የኮሌጁ ሚና በዋናነት ዲዛይን እና ክትትልን አስመልክቶ ከሰርቬይንግ እና ድራፍቲንግ የስልጠና ዘርፍ ጋር የተያያዘ ነው ለማለት ይቻላል።  በዚህ አጋጣሚ የቀድሞ ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ በሃሳብ አመንጭነትና ስራው እውን እንዲሆን ያበረከቱት አስተዋጽኦ  ያንበሳውን ድርሻ ይይዛል።  አሁን ያሉት አመራሮች ደግሞ የተጀመረውን ስራ እንዲጠናቀቅ እያበረከቱ ያሉት አስተዋጽኦ የሚደነቅ ነው ብለዋል።  የሰርቬንግና ድራፍቲንግ የስልጠና ዘርፍም በአሠልጣኝ ሚኪያስ በኩል በተነደፈው ዲዛይንና በግንባታ ክትትል ሙያዊ ስራ አሻራውን በትምሳሌትነት ያኖረ ነው። 

ከውጭም ሆነ ከውስጥ ግንባታውን የተመለከቱ የህብረተሰብ ክፍሎች ስራው ቀልብ የመግዛት አቅም እንዳለው በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲናገሩ ይደመጣል።  ቀረብ ብለውም የትምህርት ቤቱ መስራች አልጋወራሽ ተፈሪ መኮንን ያስተላለፉትን መልዕክት በማንበብ ተጨማሪ መረጃ እያገኙ እንደሆነ በቆምንባቸው  አፍታዎች ለማድመጥ ችለናል። 

በመጨረሻም አሠልጣኝ ሚኪያስ ባስተላለፈው መልዕክት ስራውን ሲያይ በጣም እንደሚደሰትበት እና ኩራትም እንደሚሰማው በመግለጽ የቤተሰቡን በተለይም የባለቤቱን ጊዜ መስዋዕት በማድረግ እገዛቸውን ስላገኘ ሊያመሰግናቸው ወዷል ፤ ይገባቸዋልም። 

ይህ ስራ የሚያስተምረን ፤ የቁርጠኛነት ጉዳይ እንጂ  ኮሌጁን እና ተጠቃሚውን የሚረዱ ስራዎች ለመስራት የሚችል በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል ስላለ ማኔጅመንቱ በማስተባበር ወደ ተግባር እንዲቀየር ጥረት ማድረግ እንዳለበት ያመላከተ በመሆኑ የማበረታቻ ስርዓት ቢበጅለት ደግሞ የበለጠ ጥሩ እንደሚሆን ሚኪያስ መልእክቱን አስተላልፏል። የዝግጅት ክፍላችንም ሚኪያስና ቤተሰቦቹን ከማመስገን ባሻገር መልእክቱ በኢንተርፕራይዝ ምስረታና ትግበራ ላይ ትኩረት ቢሰጥበት እንላለን። 

             ኮሙኒኬሽን ቡድን

.

Copyright © All rights reserved.

Created with