ሐምሌ 17/2017ዓ.ም
በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ለኮሌጁ ማህበረሰብ ቀረበ።
አፈጻጸሙ በሁለት አካላት የቀረበ ሲሆን አቅራቢዎችም የኮሌጁ ስነ-ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት እና የኮሌጁ ዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ናቸው ።
በመጀመሪያ የቀረበው የስነ-ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውና ያከናወናቸውን ተግባራት አፈጻጸም ሲሆን በተመሳሳይ በዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት የበጀት ዓመቱን ዕቅድ እና ክንውን የዓበይትእና ቁልፍ ተግባራት ክንውን በዝርዝር ቀርቧል።
በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተሳታፊዎቹ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀደም መስተካከል አለባቸው ፣ በትኩረት ሊሰራበት የሚገባቸውን ፣ በሪፖርቱ ያልተካተቱና በሚገባ ያልተዳሰሱ ያሏቸውን ሃሳብ አስተያየት አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን አቶ አብዱልበር መሐመድ በቀረበው ሪፖርት ላይ እና በተነሱ ሃሳብ አስተያየቶች በቀጥታ ሊወሰዱ ይገባል ያሏቸውን እንደ ግብአት ተወስደው መስተካከል አለባቸው ያሉትንም ደግሞ አቅጣጫ በመስጠት ስብሰባው ተጠቃሏል ።
ኮሙኒኬሽን ቡድን