የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አካል ጉዳተኛ ስልጣኞችን በአካቶ ስልጠና በማሰልጠን ፋና ወጊና ብቸኛ ከሌጅ ነው ።
ከልጁ በ2018 በጀት ዓመት ዓይን ስውራን እና ከፊል ዓይነ ስውራንን ለማሰልጠን የሚያስችል የ JAWS ሶፍት ዌር ስልጠና ከህዳሴ አካል ጉዳተኞች ማህበር ጋር በመተባበር ለአሠልጣኞች፥ለስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች፥ለሬጅስትራርና የላይብረሪ ባለሙያዎች እንዲሁም አስተባባሪዎች የ3ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል ።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ደመላሽ ተስፋዬ ምንም እንኳን የአካቶ ስልጠናን እየተገበርን ቢሆንም በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን ጠቁመው ይህንን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲያስችል ከEASE project ጋር በማስተሳሰር በመደበኛ ስልጠናውም ሆነ በአጫጭር ስልጠና ለሚመጡ አካል ጉዳተኛ ሰልጣኞች ለስልጠናው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን ለማሟላት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ወ/ሪት ቤተልሄም የፕሮጀክቱ ዓላማ አካል ጉዳተኞችን እና ሴቶችን ወደ ፊት ማምጣት በመሆኑ የአካል ጉዳተኞችን ማእከል ለማጠናከር እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለማሟላት በትጋት እንሰራለን በማለት ቃል ገብተዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የህዳሴ አካል ጉዳተኞች ማህበር ም/ስራ አስኪያጅ አቶ መዓዛኃይማኖት እና አቶ አሚድ ኮሌጁ በዚህ ልክ ትኩረት ሰጥቶ ከሰራ እኛም ያለ ምንም ቅድመሁኔታ ስልጠናዎችን በመስጠት ባለሙያዎችን የማብቃት ስራ እንሰራለን በማለት ተናግረዋል።