🇪🇹08/11/2018 ዓ.ም🇪🇹
በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ‘Ease’ ፕሮጀክት አስተባባሪነት እና ከ‘ሞአስ ኮንሰልታንት’ ጋር በመተባበር ለ2018 ዓ.ም ተመራቂ ሰልጣኞች የተዘጋጀ የሲቪ (CV) አጻጻፍ፣ የረዝሜ (Resume) ዝግጅት እና የሥራ ቃለ-መጠይቅ (Interview) ዝግጅት ዙሪያ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።
መድረኩ ተመራቂ ሰልጣኞች ከኮሌጅ ቆይታቸው በኋላ ወደ ሥራው ዓለም ሲቀላቀሉ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመወጣት የሚያስችላቸውን ተግባራዊ ክህሎት ለማስጨበጥ ያለመ ነው።
የዕለቱን መድረክ የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተመራቂዎች ከተመረቁ በኋላ ካለው የሥራ ፈላጊነት ስሜት ወጥተው በኢንዱስትሪው ውስጥ የራሳቸውን የላቀ አበርክቶ ማበርከት እንዳለባቸው አሳስበዋል። አክለውም ሰልጣኞች የሥራ ፈጠራ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸውና ለዚህም ኮሌጁ የሚያቀርበውን የንግድ ማብሰያ (Incubation Center) ድጋፍና አገልግሎቶችን በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውንና ሀገራቸውን መጥቀም ይኖርባቸዋል" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የኮሌጁ አካዳሚክ ምክትል ዲን አቶ ደመላሽ ተስፋዬ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሰልጣኞች በኮሌጅ ቆይታቸው የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር መለወጥ የሚችሉት በራስ መተማመንን ሲያዳብሩ መሆኑን ገልጸዋል።ምሩቃን በሥራ ገበያው ውስጥ ተፈላጊና ብቁ ሆነው ለመገኘት በውስጣቸው ያለውን እምቅ ችሎታ አውጥተው በመጠቀም ረገድ ጠንካራ ተወዳዳሪ መሆን እንዳለባቸው በአጽንኦት ገልጸዋል።
በዕለቱ በ‘ሞአስ ኮንሰልታንት’ ባለሙያዎች አማካኝነት ለተመራቂዎቹ ማራኪ ሲቪ እንዴት እንደሚዘጋጅ፣ በሥራ ቃለ-መጠይቅ ወቅት መደረግና መተው ስላለባቸው ስነ-ምግባሮች እና ራስን ለአሰሪዎች በተሻለ መንገድ የማስተዋወቂያ ስልቶች ላይ ሰፊ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኞችም መድረኩ ወደ ሥራው ዓለም ለመሸጋገር ትልቅ መነቃቃትን እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://vm.tiktok.com
https://t.me/EntotoPtc1917
https://youtube.com/@entototms
https://www.facebook.com
ከኮሚኒኬሽን ቡድን





.