🇪🇹24/10/2018 ዓ.ም🇪🇹
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሥር የሚገኘው የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተከናወኑ ተግባራትን የሚያሳይና በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት የተጠመረውን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለኮሌጁ ማኅበረሰብ አቅርቧል።
የኮሌጁ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ ንግሥት ገ/ህይወት በሰፊው ባቀረቡት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የኮሌጁ ማኅበረሰብ ሰፊ አስተያየትና ውይይት አድርጎበታል። በውይይቱም ወቅት አንዳንድ ማብራሪያ ለሚያስፈልጋቸው ሐሳቦች በኮሌጁ አመራሮች አማካኝነት ተገቢው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በተጨማሪም የኮሌጁ ማኅበረሰብ በቀጣይ በጀት ዓመት ተጠናክረው መሄድ በሚገባቸው የኮሌጁ ሥራዎችና በትኩረት ሊሠራባቸው በሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በስፋት ተወያይቷል።
የኮሌጁ ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ በበኩላቸው የኮሌጁ ማኅበረሰብ በበጀት ዓመቱ ለነበረው ቀና የሥራ መንፈስና ትጋት ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም የኮሌጁን አሠራርና የአገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ እንዲሁም ለማዘመን የማኅበረሰቡ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ዲኑ በመድረኩ መዝጊያ ንግግራቸው፣ የኮሌጁ ማኅበረሰብ "በየኔነት ስሜት" በሪፖርቱና በእያንዳንዱ ጉዳዮች ላይ ላሳየው ሰፊና ንቁ ተሳትፎ ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://vm.tiktok.comኸ
https://t.me/EntotoPtc1917
https://youtube.com/@entototms
https://www.facebook.com
ከኮሚኒኬሽን ቡድን



.