ሐምሌ 18/11/2017 ዓ.ም.
የተፈሪ መኮንን ስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ከአካዳሚ ኮሚሽን አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
በውይይቱ የስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበት ሲሆን ለውይይት የቀረቡት አጀንዳዎች ትኩረት እና የተሰጡ የመፍትሄ ሃሳቦች፤ መግባባት የተደረሰባቸው ጉዳዮች
በ 1ኛ አጀንዳ የ2017 ተመራቂ ሰልጣኞች የሀገር አቀፍ ምዘና ያለበትን ደረጃ የተመለከተ ሲሆን እያንዳንዱ የስልጠና ዘርፍ ተጠሪ በየስልጠና ዘርፉ በስልጠና ዘመኑ የተመራቂ ሰልጣኞች ቁጥር፤ የትብብር ስልጠናቸውን ጨምሮ ስልጠናውን ስለማጠናቀቃቸው እና ተቀማዊ ምዘና ወስደው ለሃገር አቀፉ ምዘና ዝግጁነታቸውን በተመለከተ ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በተደረገው ውይይት የአውቶሞቲቭ እና የኢንፎርሜሽን ስልጠና ዘርፍ ብቻ ስልጠና እና የተቋም ምዘና እንዲሁም ምዴል ምዘና አስመዝነው ለሀገር አቀፍ ምዘና የሰልጣኞች ዝርዝር የላኩ ሲሆን ሌሎች ስልጠና ዘርፎች በዚህ አግባብ ያላጠናቀቁ መሆኑን በጥብቅ ከተገመገመ በኃላ ቀሪ ስራዎችን እሰከ ነሐሴ አጋማሽ እንዲያጠናቅቁ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሰዋል፡፡
በ2ኛ አጀንዳ ተመራቂ ሰልጣኞች የስራ ትስስርን በተመለከተ በትኩረት የተነሳ ሲሆን ሰልጣኞች ስልጠናቸውን አጠናቀው በምዘና ብቃታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ከስራ ጋር እንዲተሳሰሩ ስራዎች ይሰራሉ፡፡ ምንም እንኩዋን የስልጠና ዘመኑ ተመራቂዎች የሃገር አቀፉን ምዘና ጀመሩት ውስን ቢሆኑም አንዳንድ ስልጠና ዘርፍ ተመራቂዎች ቀድመው ከስራ ጋር መተሳሰራቸው የስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች ገልጸው ያልተሳሰሩት ሠልጣኞች ደግሞ ስልጠናቸውን እና ምዘናውን እንዳጠናቀቁ ከስራ ጋር እንዲተሳሰሩ የተመቻቸ እነደሆነ እነዚህ የስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች ለተሰብሳቢዎች አስረድተዋል፡፡
3ኛ Ethio coder ስልጠና በሰልጣኝ በአሰልጣኝ ያለበት ደረጃ የተገመገመ ሲሆን
አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች የEthio coder ስልጠና በመውሰድ ላይ መሆናቸው በውይይቱ የተገለጸ ሲሆን፤ አወሳሰዱም በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሆኖ አንዳንዶች አራቱንም የስልጠና ፓኬጆች ያጠናቀቁ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ አንድም፤ ሁለትም ሶስትም መውሰዳቸውንና ሌሎች ደግሞ ስልጠናውን አየተከታተሉ መሆኑ ታውቋል፡፡
በውይይቱ መጨረሻም የስልጠናውን አስፈላጊነት ከተገለጸ በኋላ ሁሉም የኮሌጁ ማህበርሰብ አባላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተሰምሮበታል፡፡
4ኛ የE-School አተገባበር ያለበት ደረጃ የተዳሰሰ ሲሆን የሰልጣኞች መረጃ፤ የሚወስዱዋቸው ስልጠናዎች እና ያስመዘገቡት ውጤት በመረጃ ቋት ሰፍሮ የሚገኝ ቢሆንም በጥቂት የስለጠና ዘርፎች የተሟላ አለመሆኑ ግንዛቤ ተይዞ አስቸኳይ የእርምት እርመጃ እንዲወሰድ ከመግባባት ተደርሷል፡፡
የስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች ይህንን ስራ በማስፈጸም ስራውን እንዲከታተሉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ኮሙኒኬሽን ቡድን
.