ነሐሴ 5/2017ዓ.ም
በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች የ2017/18 በጀት ዓመት ዕቅድ እና ትግበራ ላይ ያተኮረ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ ።
የኮሌጁ ኮር አመራሮች ከዋና ዲኑ አቶ አብዱልበር መሐመድ ጋር የተፈራረሙት የስምምነት ሰነድ ያካተተው በበጀት ዓመቱ ኮሌጁ አቅዶ የሚተገብራቸው ዋና ዋና ግቦችና ተግባራት በጊዜ እና በሀላፊነት ደረጃ ተደራጅተው የተዘጋጁ መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ሥራዎች ቆጥሮ መስጠትና ቆጥሮ መቀበል በሚያስችል አገባብ የተቀመጡ ከመሆናቸውም በላይ የክትትል ሥርአት ተዘርግቶላቸዋል። አፈጻጸሙም ግልጸኝነትን በማስፈን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው ።
በአጠቃላይ ኮሌጁ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ያስችል ዘንድ በ10 ነጥቦች የተቃኘ ስልጣንን፣ ኃላፊነትን እና ተጠያቂነትን ያሰናሰነ የስምምነት ሰነድ ከስልጠና ጉዳዮች አስተባባሪ፣ ከተቋማትና አሠልጣኝ ልማት ም/ዲን ፣የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ም /ዲን እንደዚሁም ከሽሮ ሜዳ ካምፓስ ም/ዲን ጋር ተፈራርመዋል።
በተመሳሳይ እያንዳንዱ ተፈራራሚ በስሩ ከሚገኙት በየደረጃው ካሉት አካላትና አባላት ጋር የሚተገበር ዕቅድና አተገባበሩን ያካተተ የስምምነት ሰነድ አዘጋጅቶ በመፈራረም ወደ ስራ እንደሚገባ ለመረዳት ተችሏል፤ይጠበቃልም።
ኮሙኒኬሽን ቡድን