በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለቴክስታይልና ጋርመንት የስልጠና ዘርፍ ሰልጣኞች በዘርፉ ትራንስፎርሜሽን (የለውጥ ጉዞ) ላይ ያተኮረ ሰፊና ጠለቅ ያለ ስልጠና ተሰጠ።
ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ስልጠና ሊዘጋጅ የቻለው በኮሌጁ የአልሙናይ (የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር) ፕሬዘዳንት አቶ ደጀኔ ግብዣ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት ደግሞ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና እውቀት ያላቸው ታዋቂው ሌክቸረር ዶክተር ያንግ ያኔ ናቸው።
ዶክተር ያንግ ያኔ ካካበቱት ሰፊ ዓለም አቀፍና ተግባራዊ ልምድ በመነሳት በቴክስታይልና ጋርመንት ትራንስፎርሜሽን ዙሪያ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ስልጠናው የዘርፉ ትራንስፎርሜሽን አስፈላጊነት ፣ የቴክስታይልና ጋርመንት ዘርፍ በወቅታዊው የዓለም ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል ለምን መለወጥና መዘመን እንዳለበት፤የእሴት ሰንሰለትና ዘላቂነት ፣ ከጥሬ ዕቃ አቅርቦት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ምርት ድረስ ያለውን የእሴት ሰንሰለት መፈተሽና ለአካባቢ ጥበቃና ለዘላቂነት ትኩረት መስጠት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ፤የስትራቴጂክ ማዕቀፍ አራት የለውጥ አቅጣጫዎች ማለትም የጥሬ ዕቃ ፈጠራ ፣ ዘመናዊና ብልህ ማኑፋክቸሪንግ ፣ አረንጓዴ ልማትና ማኅበራዊ አካታችነት ላይ አተኩሯል ።
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ ባደረጉት ንግግር ለሰልጣኞቹ ጠቃሚና ወቅታዊ እውቀት እንዲቀስሙ ይህንን ዕድል ላመቻቹት ለኮሌጁ አልሙናይ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ደጀኔ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
ዋና ዲኑ አክለውም እጅግ ጠቃሚና ተግባራዊ እውቀት ላካፈሉት ለዶ/ር ያንግ ያኔ የላቀ አክብሮታቸውን የገለጹ ሲሆን ኮሌጁ በቀጣይም በቅርበት አብሮ ለመስራትና ልምድ ለመለዋወጥ ኮሌጁ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አስታውቀዋል።
ይህ ስልጠና የኮሌጁን ሰልጣኞች የንድፈ-ሀሳብና የተግባር እውቀት ከማበልጸጉም በላይ ተቋሙ ከዓለም አቀፍ ባለሙያዎችና ከቀድሞ ተማሪዎቹ ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://vm.tiktok.com
https://t.me/EntotoPtc1917
https://youtube.com/@entototms
https://www.facebook.com
ከኮሚኒኬሽን ቡድን





.