Announcement እንኳን ደስ ያለን ! ሲጠበቅ የነበረው የጥረታችን ውጤት በእጃችን ገብቷል።

እንኳን ደስ ያለን ! ሲጠበቅ የነበረው የጥረታችን ውጤት በእጃችን ገብቷል።

02nd August, 2025

ሐምሌ 25/2017ዓ.ም

የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2018 Educational Organization Management System /የአሰራረ ስርዓትን ለመተግበር ታህሳስ 9 ቀን 2016ዓ.ም ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር ስምምነት ተፈራርሞ ስራውን ጀምሯል ፤ ከግንቦት 29/ቀን 2016 ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ  ትግበራውን መጀመሩ አብስሯል። 

በመቀጠልም እልህ አስጨራሽ የትግበራና የግምገማ ሂደቱን በመሻገር ኮሌጁ 21001:2018 Educational Organization Management System ሰርተፍኬቱን በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ተስማሚነነት ምዘና ድርጅት ኃላፊ ኢንጂነር መዓዛ አበራ እጅ ተረክቧል። በርክክቡ ወቅት ክብርት ኃላፊዋ ISO   21001:2018 Educational Organization Management System ን ተግባራዊ ያደረጉ ኮሌጆች በኢትዮጵያ  3 ብቻ  ሲሆኑ እንደ ከተማ ደግሞ ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2ኛው ኮሌጅ መሆኑን ጠቅሰው  በዚህ የዕውቅና ሰርተፊኬት ኮሌጁ በተለያዩ ደረጃዎች የመወዳደር ፣ እራሱን የመሸጥ እና ማስተዋወቅ የሚችልበት ሁኔታ የሚፈጥርለት  መሆኑን አመላክተው በድጋሚ  እንኳን ደስ ያላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። 

በሰርተፊኬት ርክክቡ ላይ የኮሌጁ ዲን አቶ አብዱልበር መሐመድ ድርጅቱ ከቅድመ ዳሰሳ ጥናት ጀምሮ በሰነድ ዝግጅትና ክትትል እንዲሁም በምዘና ሂደቱ ለነበረው ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ ድርጅቱ ከሚሰጣቸው በርካታ አገልግሎቶች አንጻር በጋራ የምንሰራቸው ስራዎች እንደሚኖሩ ጠቁመው በሁሉም ደረጃዎች ለኮሌጁ የተመደቡ ባለሙያዎች በመልካም ስነ-ምግባራቸው ከልብ የሚከታተሉን እና የሚደግፉን ነበሩ ለዚህም በግላቸው እና በኮሌጁ ስም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።  በዚህ አጋጣሚ በዚህ ስራ ላይ ለተሳተፉና ለኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ ያለን ብለዋል። 

በተመሳሳይ የኮሌጁ የበላይ አመራሮች እና አስተባባሪው አቶ ሚካኤል ጎኣ  ኮሌጁ ያለውን አቅም በመግለጽ ከድርጅቱ ጋር ለነበረው ቆይታ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። 

                      ኮሙኒኬሽን ቡድን

.

Copyright © All rights reserved.

Created with