በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማርኬቲንግ የስልጠና መስክ ተመራቂዎች የእናመሠግናለን ፕሮግራም አዘጋጅተው አሠልጣኞቻቸውን ሲያመሠግኑ የዝግጅት ክፍላችን በቦታው ተገኝቶ ነበር።
በተለያዩ ዝግጅቶች የደመቀው የእናመሠግናለን ፕሮግራም ለዚህ ደረጃ እንዲበቁ አስተዋጽኦ ያደረጉ አሠልጣኞች ተሸልመውበታል፣ የግጥም ውዳሴ አግኝተውበታል ። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የስልጠናና አካዳሚክ ም/ዲን አቶ ደመላሽ ተስፋዬ ሠልጣኞቹ ስላደረጉት ነገር አመስግነው ሠልጣኞች ከምርቃታቸው በፊት በቀጣይ የስልጠና ማጠናቀቂያ ምዘናቸውን በአግባቡ እንዲዘጋጁና እና እንዲወጡ መልእክት አስተላልፈው ሠልጣኞች ያዘጋጁትን ስጦታ ለአሠልጣኞቹ አበርክተዋል።
በተመሳሳይ የስልጠና ዘርፍ ተጠሪው አቶ አለማየሁ ተስፋዬ እና አሠልጣኞቹ ለተበረከተላቸው ስጦታ ምስጋናቸውን አቅርበው ሰልጣኞች ለምዘና በሚኖራቸው ዝግጅት የበኩላቸውን በማበርከት ለውጤት እንዲበቁ እንሰራለን በማለት ቃል ገብተዋል። አያይዞም ከስራ ጋር የማስተሳሰሩን ስራ አጠንክረው እንደሚሰሩ አቶ አለማየሁ ተስፋዬ ተናግረዋል ።
ይህ የእናመሠግናለን ፕሮግራም በማርኬቲንግ ሠልጣኞች ሲደረግ ለመጀመሪያ ግዜ ሳይሆን ቢያንስ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ዝግጅት እንደነበር እናስታውሳለን፤ለአሠልጣኞቹ የሞራል ስንቅ ስለሚሆን ተበራተው እንዲሰሩ የበኩሉን አስተዋጽኦ ይኖረዋል የሚል እምነት አለን።
እኛም መልካም የሽግግር ጊዜ ለሠልጣኞች ተመኘን።
ኮሙኒኬሽን ቡድን