Announcement በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የበጀት ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተከናወነ።

በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የበጀት ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተከናወነ።

01st August, 2025

ሐምሌ 22/2017ዓ.ም 

በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የበጀት ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተከናወነ። 

ከአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የተላከው የባለሙያዎች ቡድን በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተገኝተው የ2017ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሂደዋል ። በግምገማው የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት በዋነኛነት በኮሌጁ ከታቀዱት ተግባራት አንጻር ያለውን አፈጻጸም ምን ይመስላል?? ሌሎች በየዘርፋቸው ባስቀመጡት ዕቅድ መነሻነት ክንውኑ እና ሂደቱ ምን ይመስላል? እሚለው እና በሰነድ የታገዘ መሆን አለመሆኑን የተፈተሸ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማብራሪያ በመስጠት ተሳትፎ አድርገዋል። 

በግምገማው አብዛኛው የኮሌጁ ዕቅድ መሆን በሚገባው ልክ የተፈፀመ ቢሆንም አንዳንድ ከመረጃ አያያዝ ጋር የተያያዙ ክፍተቶች መታየቱን ተከትሎ የኮሌጁ ዲን አቶ አብዱልበር መሐመድ ክፍተቱን ለመሙላት በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ለገምጋሚ ቡድኑ አስረድተው በግምገማው ለነበራቸው ቆይታ ባለሙያዎቹን አመስግነዋል። 

          ኮሙኒኬሽን ቡድን

.

Copyright © All rights reserved.

Created with