ሐምሌ 30/2017ዓ.ም
የE-school ትግበራን አስመልክቶ
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የE-school ሲስተም ምንድ ነው ? E-school ሲስተም ምን ምን ጉዳዮችን ይይዛል? ምን ጠቀሜታስ አለው ? በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ለኮሌጁ አሠልጣኞች ፣አስተባባሪዎች፣ የሬጅስትራር ባለሙያዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተዘጋጅቷል።
E-school ሲስተም ከመማር ማስተማሩ ባሻገር አስተዳደራዊ ስርዓትን ውጤታማ የሚያደርግ ፕላት ፎርም በመሆኑ አሰራርን ለማዘመን፣ተደራሽ ለማድረግና የክፍለ ዘመኑን አሰራር በመቀላቀል ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል። ስራው በሚፈለገው ልክ ተግባራዊ እንዲሆን ለማስቻል በቀጣይ በየስልጠና ዘርፉ ለሁሉም አሰልጣኞች ስልጠናው ተጠናክሮ የሚሰጥ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ።
በስልጠናው ማጠናቀቂያ በነበረው ውይይት የስልጠናው አቀራረብና አስፈላጊነት ከመዘግየቱ ውጪ አጠያያቂ አይደለም ያሉት ተሳታፊዎቹ በየስልጠና ዘርፉ ያለው የኮምፒውተር እጥረት እና የኔትወርክ ተደራሽነት ለውጤታማነቱ ተግዳሮት እንዳይሆን ከወዲሁ ቢታሰብበት በማለት አስተያየት ተሰጥቷል።
ኮሙኒኬሽን ቡድን