Call us:
+251912070000
|
Mail us for help:
entotopolytech@aatvetb.edu.et
|
Help center
360° Support - We are here to assist you.
Teferi Mekonnen Polytechnic College
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
Support
Back
Support
Submit Ticket
My Tickets
More
Service
About
Contact Us
Status
Login
Announcement
በተፈሪ መኮንን ፖ/ቴ /ኮሌጅ ታላቅ የስራ እድል ትስስር (Job Fair) ተካሄደ።
በተፈሪ መኮንን ፖ/ቴ /ኮሌጅ ታላቅ የስራ እድል ትስስር (Job Fair) ተካሄደ።
16th July, 2026
#ካባ_መልቲሚዲያ
በቅርቡ መቶኛ አመቱን ያከበረው እና አለምአቀፉን የ የ ISO 210001 የጥራት ሰርትፍኬት ያገኘዉ አንጋፋው ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሰልጣኞች የስራ ትስስር ለመፍጠር በርካታ ተቋማት የተሳተፉበት አውደ ርዕይ አዘጋጀ ።
በዕለቱም የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ ፣ የኮሌጁ ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ ፣ ከተለያዩ የቴ/ሙ የመጡ የኮሌጅ ዲኖችና አመራሮች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ከ30 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶች ተገኝተዋል ።
መርሀግብሩ ተመራቂ ተማሪዎችን በቀጥታ ከቀጣሪዎቻቸው ጋር ለማገናኘት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ሰልጣኞች የክህሎት ልውውጥ በማድረግ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ማለትም በሆቴል ፣ በአይሲቲ ፣ ፋይናንስ ፣ ኤሌክትሪክ እና እንጨት ስራ አምራቾች ፣ አረንጓዴ ቴክኖሎጅ ፣በጋርመንትና ፣ በሌሎች የሙያ ዘርፎች ላይ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር እንዲገናኙ እድሎች ተመቻችተዋል።
በቀጣይም እንዲህ ያሉ የስራ ትስስሮች በቋሚነት እንደሚደረጉ የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ በተደረጉት ግንኙነቶች በርካታ ሰልጣኞች የስራ እድል እንዳገኙም ገልፀዋል። ዲኑ አክለዉም ይህ ሁነት እንዲዘጋጅ የተባባሩ አካላትን በተለይም ደግሞ EASE ፕሮጀክትን በተለየ ሁኔታ ያመሰገኑ ሲሆን ይህ ሁነት በቀጣይም በስፋት እንደሚደረግ ገልጸዋል።
#ካባ_መልቲሚዲያ
.