Announcement በተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የTTLM ቫሊዴሽን እና የEASE ፕሮጀክት የ4ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ለአድቫይዘሪ ቦርዱ ቀረበ።

በተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የTTLM ቫሊዴሽን እና የEASE ፕሮጀክት የ4ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ለአድቫይዘሪ ቦርዱ ቀረበ።

07th July, 2026

ሰኔ 27/10/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ— በተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE  ፕሮጀክት አማካኝነት የተዘጋጁ የማሰልጠኛ ሰነዶች (TTLM) የቫሊዴሽን ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለአድቫይዘሪ ቦርድ አባላት ቀረበ።
ኮሌጁ በእስቴቲክስ (Aesthetics) የትምህርት ክፍል ስር የሚገኙትን የቲያትር፣ የፔንቲንግ፣ የግራፊክስ እና የስክላፕቸር (ቅርጻ ቅርጽ) የሙያ መስኮችን የማሰልጠኛ ሰነዶች (TTLM) የቫሊዴሽን ሥራ በተሳካ ሁኔታ አከናውኗል።
ይህ የሥልጠና ሰነድ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ እና ከተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች በጋራና በትብብር ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል።
የቫሊዴሽን መድረኩ ዓላማ የሥልጠና ሰነዶቹ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ፣ የገበያውን ፍላጎት ያማከሉና ሰልጣኞችን በተግባራዊ እውቀት ብቁ የሚያደርጉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ነው።
በተያያዘ ዜና የ4ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ለአድቫይዘሪንግ  ቦርዱ ቀርቧል
ከዚሁ ጎን ለጎን፣ የኮሌጁ የEASE ፕሮጀክት የ2018 በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለአድቫይዘሪ ቦርዱ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ቦርዱ በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን፣ የተመዘገቡ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በጥልቀት ገምግሟል።
በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ከተደረገ በኋላ፣ የአድቫይዘሪ ቦርድ አመራሮች እና የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ በጋራ ባስተላለፉት መልዕክት፡ "የEASE ፕሮጀክት በበጀት ዓመቱ በጣም ጥሩ አበረታች አፈጻጸም አሳይቶታል ይሄ ስኬት ሊመዘግብ የቻለዉ በባለድርሻ አካላት ከኮሌጁ ማህበረሰብ  ጋር ከEASE ፕሮጀክት አስፈጻሚዎች ጋር ጠንካራ ትብብር ነዉ ብለዉ የገለጹ ሲሆን" ለሚቀጥለዉ በጀት ዓመት ከዚህ በበለጠ በቅንጅት በተባበረ መንፈስ የተጀመረዉን ስኬት አጠናክረን ማስቀጠል ይኖርብናል ሲሉ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል።
የዕለቱ መርሃ ግብር የEASE የፕሮጀክትን አፈጻጸም ውጤታማነት በማድነቅ እና ለቀጣዩ በጀት ዓመት ይበልጥ ስኬታማ ሥራዎችን ለመስራት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with