ሐምሌ 24/2017ዓ.ም
7ኛ ዙር ሃገራዊ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ10,000 በላይ ችግኞችን በመትከል ተከናውኗል። "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ሃገራዊ ተልዕኮን በማንገብ የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮር አመራሮች፣የማኔጅመንት አባላት፣አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት፣ የቡድን መሪዎች እና አስተባባሪዎች የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ካራ መድኅኒዓለም ቤ/ክርስቲያን አካባቢ በተዘጋጀው ስፍራ ተከናውኗል።
በችግኝ ተከላው መርሃ ግብር ላይ የኮሌጁ ዲን አቶ አብዱልበር መሐመድ ባስተላለፉት መልእክት በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ላይ በመሳተፍ ምህዳርን ለማስጠበቅ አሻራችንን ለማኖር በመቻላችን ኩራት ይሰማናል፤ ለቀጣዩ ትውልድ የምናወርሰው አንዱ ስጦታችን መሆን አለበት በማለት ይህ እውን እንዲሆን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አሁን ላይ የተከልነውን ችግኝ ተመልሰን በመጎብኘትና በመንከባከብ ልንከታተለው ይገባልም ብለዋል።
የዝግጅት ክፍላችንም ይህን ሃሳብ በመጋራት በክትትሉ እና በእንክብካቤው ስራ ዳግም ያገናኘን ብለናል።
ኮሙኒኬሽን ቡድን